የመጀመሪያዋና መጨረሻዋ ስለሆንኩ
የተከበርኩና የተናቅኩ
ጋለሞታና ቅድስት
ሚስትና ድንግል ፤ ልጅና እናት፡፡
የናቴ የተዘረጉ ክንዶች
መካንና ልጆቼም ብዙዎች፡፡
ባለትዳር እንዲሁም ሳዱላ
ወላድና ልጅአልባ፤ የወሊድ ህመምም ከለላ፡፡
ሚስትም ነኝ ባልም ነኝ
ባሌም እኔን የፈጠረኝ
የባሌም እህት እኔው ነኝ
እሱም የተገፋው ልጄ፡፡
ስለዚህ ሁሌም አክብሩኝ
ወራዳና ድንቅም ስለሆንኩኝ፡፡
በ3ኛ/ 4ኛው ክ/ዘ የተጻፈ እና ናግ ሃማዲ፤ግብጽ ውስጥ በቁፋሮ የ ተገኘ፡፡
ትርጉም: በ ብርሃነ ሃይለስላሴ
የካቲት 2003 እ/ኢ/አ
መታሰቢያዋ ለሴቶች: (አያት፣እናት፣ሚስት፣እህት፣ልጅ) ለ ሆናችሁን በሙሉ ትሁንልኝ።
Saturday, February 19, 2011
Hymn to Isis (ማህሌተ አይሲስ)
Labels:
amharic poem,
Birhane Hailesilassie,
Ethiopia,
ethiopian art,
hymn for isis,
isis,
ሴት,
ብርሃነ ሃይለስላሴ,
እናት,
ግጥም
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
what do you do for living? (just curious, am not being sarcastic).
ReplyDelete